ባሁን ግዜ የተለያዩ በእንተርኔት የሚሰሩ የኦንላይን ስራዎች በጣም እየተለመደ መቷል። ምክንያቱም በትርፍ ሰዓት ስለሚሰሩና ወዴትም መንቀሳቀስ ሳያስፈልገን ቤት ተቀምጠን መስራት ስለሚቻል ብዙዎች ተጨማሪ የገቢ ምንጫቸው አድርገውታል አሁን። እርሶስ ይህን እድል በመጠቀም ተጨማሪ የገቢ ምንጭ መፍጠር አይፈልጉም? በርግጥም ይፈልጋሉ, ስለዚ ይህን ፅሁፍ እስከመጨረሻ ያምብቡት።

እንዴት የዩቱብ ቻናል ከፍተን ገንዘብ መስራት እንችላለን
ገንዘብ መስራት

በዩቱብ እንዴት ገንዘብ ማግኘት እንችላለን

በኦንላይን ገንዘብ ለመስራት ብዙ መንገዶች ብኖሩም በዚን ግዘ ግን በከለማቺን ላይ በጣም የብዙዎች ምርጫና የብዙዎች የገቢ ምንጭ የሆኑት በዩቱብ ላይ ቪድዮ በመስራት ከቪድዮ ማስታወቅያ ላይ የሚገኘውን ገቢ ማግኘትና ሌላኛው የኦንላይን ስራ ደግሞ የብሎግ/ዌብሳይት/ ስራ ነው። ለዛሬም ፕሮግራሜ ከላይ ከጠቀስኳቸው አንዱን ማለትም እንዴት ዩቱብን በመጠቀም የገቢ ምንጭ መፍጠር እንደምንችን ሙሉ በሙሉ ከመጀመርያ ጀምሮ ያሉት ነገሮች እናያለን።

በዚ ፕሮግራም የምናያቸው ዋና ዋና ነገሮች

  • ዩቱብ ቻናል ለመክፈት ምን ያስፈልጋል
  • ➨ቻናል ከመክፈታቺን በፊት ማወቅ ያለብን የዩቱብ ህጎች
  • ➨ዩቱብ ቻናል እንዴት ይከፈታል
  • ➨ለዩቱብ ቻናላቺን የሚያስፈልጉን መተግበርያዎች
  • ➨በዩቱብ እንዴት ተመልካቾችን ማግኘት ይቻላል
  • ➨የዩቱብ ቻናላቺንን ገቢ/ገንዘብ/ እንዲሰራ ለማድረግ
  • ➨ዩቱብ ላይ የሰራነውን ገንዘብ እንዴት እንቀበል

1.ዩቱብ ቻናል ለመክፈት ምን ያስፈልጋል

ብዙ ሰዎች ከዩቱብ ላይ በርካታ ገንዘብ ይገኛል ብሎ ስለሚያስቡ ብቻ ዩቱብ ቻናል ይከፍታሉ። አው ልክ ነው ከዩቱብ ላይ በርካታ ገንዘብ ይገኛል ነገር ግን ይህ ህልማችሁ እንዲሳካ ከፈለጋች አስቀድማችሁ ይህን ነገር ማድረግ አለባችሁ። የዩቱብ ቻናል ከመክፈታችሁ በፊት ችሎታችሁ ምን ላይ እንደሆነና የራሳችሁን የተፈጥሮ ወይም በትምህርት ያገኛችሁትን ችሎታችሁን ለይታችሁ አውጡትና ይህን ችሎታችሁን ለህዝብ ለማካፈል ተዘጋጁ። ምክንያቱም ወደ ዩቱብ ስትመጡ ከበጣም በርካታ ዩቱበሮች ጋር ነው ምትፎካከሩት ።ነገር ግን የራሳችሁ እውቀት ብቻ ለሰው ለማካፈል ከመጣችሁ ሁልግዜም ተወዳጅና ልዩ ሰው እንደሆናችሁ ትቆያላችሁ።

2.የዩቱብ ቻናል ከመክፈታቺን በፊት ማወቅ ያለብን የዩቱብ ህጎች

አሁን ልክ ተራ ቁጥር አንድ ላይ ባያችሁት መሰረት የራሳችሁን ችሎታ አውቃችሁታል። የዩቱብ ቻናልም ለመክፈትና ለመጀመር ወስኗል። ስለዚ አስቀድማችሁ ማወቅ ያለባችሁ የዩቱብ ህጎች አሉ። መቼም ያው የዩቱብ ቻናል ስንጀምር ገና ወደ አእምኣቺን የሚመጣው ገንዘብ ማግኘት ነው። ነገር ግን በዩቱብ ገንዘብ ለማግኘት እነዚ የዩቱብ ህጎችን አስቀድመን ማወቅ አለብን።

4000 የእይታ ሰዓትና 1000 ተከታዮች/Subscribers- ልክ የዩቱብ ቻናል ከፍተን ቪድዮ መጫን እንደጀመርን ቻናላቺን ገንዘብ መስራት አይጀምርም። የዩተብ ቻናላቺን ገንዘብ መስራት የሚጀምረው ባለፉት 12 ወራት or 365 ቀናት ውስጥ 4000 የእይታ ሰዓትና 1000 ተከታዮችን ማግኘት አለበት። ብዙ ሰዎች ይህን ነገር ስያዩ ይወዛገባሉ። ብዙዎች በ 12 ወራት 4000 ሰዓት የምለው ህግ የተገደበ የግዜ ገደብ ስለሚመስላቸው በተባለው ግዜ ማሳካት ካልቻሉ ተስፋ ይቆርጣሉ። በ 12 ወራት 4000 የእይታ ሰዓት ማለት አሁን ካላችሁበት ቀን ወደኋላ 365 ቀናት ማለት ነው። ለምሳሌ የዩቱብ ቻናል የጀመራችሁ ከ 16 ወራት በፋት ከሆነ ለናንተ የሚያገለግለው ግዜ የመጨረሸዎቹ 12 ወራት ብቻ ናቸው, የመጀመርያዎቹ 4 ወራት አይቆጠሩም ማለት ነው።

3. የዩቱብ ቻናል እንዴት ይከፈታል

የዩቱብ ቻናል መክፈት ከመጀመራቺን በፊት ኢሜል ወይም የጂሜል አካወንት ያስፈልገናል። ከዚ ቀደም የከፈታችሁት ጂሜል አካወንት በስልካችሁ ውስጥ ከሌሌ በፍጥነት ወደ ስልካችሁ ሴቲንግ በመግባት አዲስ የጂሜል አካወንት ይክፈቱ። በስልካችሁ የከፈታችሁት ጂሜል በራሱ ግዜ ለዩቱብም ስለሚያገለግል በቀጥታ ወደ ዩቱብ ቻናል አከፋፈቱ መሄድ እንችላለን። የዩቱብ ቻናል መክፈት በጣም ቀላል ነው, በስልክም ሆነ በኮምፒዩር የዩቱብ ቻናል ለመክፈት ስልካቺን ወይም ኮምፑየተራቺን ላይ ያለውን የዩቱብ መተግበርያ በመጠቀም መክፈት እንችላለን።

4. ለዩቱብ ቻናላቺን የሚያስፈልጉን መተግበርያዎች

አንድ የዩቱብ ቻናል የከፈተ ሰው በማንኛውን ስልኮችና ኮምፕዩተሮች ላይ ካለው ዋናው የዩቱብ መተግበርያ በተጨማሪ ሌሎች በጣም ተቃሚ የሆኑ ተጨማሪ መተግበርያወች ለስልክም ለኮምፕዩተርም ያስፈልጋሉ። እነዚ መተግበርያዎች እንደሚከተለው ተቀምጧል

1ኛ: Google chrome app. ይህ መተግበርያ በአምዛኞቹ ዘመናዊ ስልኮች ላይ ቀድሞውኑ ያለ ሲሆን በስልካቺን ላይ ከሌሌ ደግሞ ከ Playstore በማውረድ መጠቀም ይቻላል። ይህ መተግበርያ ጥቅሙ የዩቱብ ቻናላቺንን ልክ እንደ ኮምፕዩተር እይታ አድርገን እንድንጠቀምና ባጠቃላይ የዩቱብ ስቱድዮን ለመቆጣጠር ይጠቅማል

2ኛ: Kinemaster app : ይህ መተግበርያ ለቪድዮ ኤዲቲንግ የሚጠቅን አስደናቂ የስልክ መተግበርያ ነው። መተግበርያውን ከዚ ሊንክ ያውርዱ። Download

3ኛ: Pixellab: ይህ መተግበርያ ለፎቶ ማቀናበርያ የሚያገለግል አስደናቂ የስልክ መተግበርያ ነው። ከዚ ሊንክ ያውርዱ። Download

እንደ ጀማሪ ዩቱበሮ ለግዜው ከላይ የተጠቀሱ መተግበርያዎች በቂ ናቸው ነገር ግን ሌሎችም ጠቀሚ መተግበርያዎች በሌላ ፕሮግራሜ ኣቀርብላቿለሁ።

5. ለዩቱብ ቻናላቺን ተመልካች እንዴት እናገኛለን

በዩቱብ ላይ ተመልካቾችን ለማግኘት በርካታ ዘዴዎች ቢኖሩን ግን ሁሉም ነገር ሚወሰነው በተመልካች ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ነው። ምክንያቱም የመረጥነው ርዕስ ወይም topic ይወስናል። ለምሳሌ ህዝብ በብዛት ምን ማየት እንደሚፈልግ ማወቅ አለብን። በጣም አስተማሪ ቪድዮ ብቻ ስለ ሰራን ተመልካች ላናገኝ አንችልም። ከዚም በተጨማሪ በዩቱብ ተመልካች ለማግኘት ከሚረዱን ነገሮች ወሳኞቹ ለቪድዮቻቺን የምንመርጠው ርዕስና ታግ በጣም አስፈላጊ ናቸው።

6.የዩቱብ ቻናላቺንን ገቢ/ገንዘብ/ እንዲሰራ ለማድረግ

ከላይ የተጠቀሱትን ነገሮች በሙሉ ካሟላችሁና 4ሺ ሰዓትና 1ሺ ተከታዮችን ካገኛችሁ, ከዩቱብ ኢሜል ይላክሎታል በዚን ግዘ ቻናላችሁን አድሴንስ ከሚባል ገንዘብ አስተላላፊ ድርጂት ጋር ቻናላችሁን የሚታገናኙበት ግዜ ላይ ስለ ደረሰሳችሁ ቻናላችሁን አፕላይ ታደርጋላችሁ። ቻናላችሁ ተገምግሞ ለማስታወቅያ ብቁ ከሆነ በ 36 ሰዓት ውስጥ ምላሽ ታገኛላችሁ። ቻናላችሁ ብቁ ሆኖ ።ከተገኘ በቀጥታ የተያዩ ማስታወቅያዎች በቪድዮቻችሁ ላይ መታየት ይጀምሬሉ። ነገር ግን ቻናላችሁ ብቁ ሆኖ ካልተገኘ የተለያዩ መስተካከል ያለባችሁን ነገሮች እንድታስተካክሉ ዩቱብ ሌላ እድል ለወር ቀጠሮ ይሰጦታል።

7. ዩቱብ ላይ የሰራነውን ገንዘብ እንዴት እንቀበል

ልክ ቻናላቺን ገንዘብ መስራት እንጀመረ አድሴንስ አካወንታችሁ ላይ ገንዘብ መጠራቀም ይጀምራል። የተጠራቀመው ገንዘብ 10$ ስሞላ መጀመርያ ቻናላችሁን አፕላይ ስታደርጉ በሞላችሁት ከድራሻ 6 ድጂት ፒን በፖስታ ቤት ይላክላቿል። ልክ ፒኑን አግንታችሁ ቬሪፋይ ካደረጋችሁ በኋላ ገንዘባችሁ ለመቀበል ትችላላችሁ። ያንን ለማድረግ ግን መጀመርያ የገንዘብ መቀበያ መንገዱን ባንክ ትራንስፈር/ Bank Transfer method/ በማድረግ የባንክ አካወንታችሁን መሙላት ይጠበቅባቿል።

ውድ አንባብያን ስላነበባችሁ ከልብ አመሰግናለሁ። ሀሳብ አስታይት ካላችሁ ከታች በለው ሳጥን ኮመንት ይፃፉ እንዲሁም ለሌሎች ሼር ያድርጉ።